የDC Public Charter School Board ስራው ምንድን ነው?

ዓላማችን የDC ተማሪዎችና ቤተሰቦች ጥራት ባለው የሕዝብ ቻርተር ት/ቤት እንደሚገለገሉ ማረጋገጥ ነው። ይህንም የምናደርገው ጥብቅ የትምህርት መስፈርትን በማስቀመጥ፣ ሰፊ የቻርተር አፕሊኬሽን ግምገማ ሂደት በማካሄድና በመከታተል፣ አስፈላጊ ድጋፍ በመስጠት፣ ቤተሰቦችን፣ የት/ቤት ሃላፊዎችን፣ ማህበረሰቡን እና መርህ ነዳፊዎችን በማሳተፍ ነው። የDC Public Charter School Board (DC PCSB) የተሻሻለውን የDC School Reform Act of 1995 ትከትሎ በ1996 ዓ.ም. ተመሰረተ። 2006 ዓ.ም. የDC State Board of Education (BOE) የአስተዳደር ስልጣናቸውን ወደኛ ያሸጋገሩበት ነው። የሕዝብ ቻርተር ት ቤቶች ገለልተኛ ፍቃድ ሰጪ እንደመሆናችን መጠን የሕዝብ ቻርተር ት ቤቶችን ትምህርታዊ እና በጀታዊ እንቅስቃሴ እንገመግማለን፤ ት ቤቶቹም የአውራጃውንና የፌዴራል ህጎችን እየተከተሉ መሆኑን እናረጋግጣለን።