የቻርተር ግምገማ ምንድን ነው?

ቻርተር ግምገማ ማለት በSchool Reform Act (SRA) መሰረት የአንድን ት/ቤት ትምህርታዊ አካሄድ፣ የህግ ተካታይነቱን እና የበጀት አጠቃቀሙን የሚመዝን ነው። የDC Public Charter School Board (DC PCSB) ከላይ የተጠቀሱትን መለኪያዎች ተጠቅሞ የት/ቤቱን ግምገማ ሪፖርት ያቀርባል፣ መድምድሚያም የት/ቤቱን ቻርተር ቀጣይነትና አለመቀጠሉን መወሰን ነው። እንዚህ ግምገማዎች የሚካሄዱት በት/ቤቱ 5ኛ እና 10ኛ የአገልግሎት ዓመት ላይ ነው።