የቻርተር ት/ቤት ምንድን ነው?

ቻርተር ት/ቤቶች አዳዲስ ነገር ለማከናወን ነጻ ፍቃድ ያላቸው እንድሁም ለተማሪ ውጤት ተጠያቂነት ያላቸው ገለልተኛ የሕዝብ ት/ቤቶች ናቸው። በሕዝብ ድጎማ የሚንቀሳቀሱ፣ ከክፍያ ነጻ እና ከወገንተኝነት ነጻ የሆኑ ናቸው። ከድሮ የሕዝብ ት/ ቤቶች በተመሳሳይ ለሁሉ የDC ነዋሪዊች ክፍት ሲሆኑ፤ ድጎማ የሚያገኙትም በተመዘገበው ተማሪ መጠን ነው። አንድ የሕዝብ ቻርተር ት/ቤት በውጪው፣ በአስተዳደሩ፣ በሰራተኞቹ እና በማስተማሪያ ዘዴው ላይ ሙሉ በሙሉ ስልጣን አለው።