የቻርተር ማመልከቻ ተቀባይነት የማያገኝበት ምክንያት ምንድን ነው?

የአዳዲስ ቻርተር ማመልከቻዎችን ተቀባይነት ለማረጋገጥ ቦርዱ ጥብቅ የሆነ መስፈርት ይከተላል። ዓላማችን በአውራጃው ለሚገኙ ቤተሰቦች ጥራት ያላቸው ት/ቤቶችን ማቅረብ ነው። አንድ ቻርተር ተቀባይነት እንዲኖረው በአፕሊኬሽኑ ላይ የተዘረዘሩትን መመሪያዎች በጠቅላላ ማሟላት አለበት። ከትልዕኳችን እና ከፍልስፍናችን ጋር የተያያዘ እንዲሁም የት /ቤቱን ወይም የአካባቢውን ማህበረሰብ ፍላጎት ጠንቅቆ የሚያሳይ መሆን አለበት። ጉልህ ሕዝቦችንም ማካተት ይኖርበታል። መስራች አካላትም የሕዝብ ቻርተር ት/ቤት ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ፣ የምስረታ እቅዱም ለተቀባይነት እስኪደርስ በየጊዜው እንድሚያዳብሩት በቂ የሆነ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።