የቦርዱ አባላቶች እነማን ናቸው የሚመረጡትስ እንዴት ነው?

DC PCSB በከንቲባው ተመርጠው በቀረቡ እንዲሁም በDC Council ምክርና ፈቃድ በታገዙ ሰባት የቦርድ አባላት ይተዳደራል። ይህ ባለ ሰባት አባል ቦርድ ለአዲስ ት/ቤቶች ፍቃድ ይሰጣል፣ በስራ ላይ ያሉ ት /ቤቶችን ይቆጣጠራል እንዲሁም ከአፈጻጸም ግባቸው ላይ መድረስ ያልቻሉ ት/ቤቶችን ቻርተር ይሽራል።