የሕዝብ ቻርተር ት ቤቶች ለፋሲሊቲ የሚሆን ድጎማ ከከተማው ይቀበላሉ?

አዎ። የሕዝብ ቻርተር ት/ቤቶች ለፋሲሊቲ የሚውል፣ በእያንዳንዱ ተማሪ ልክ የሆነ $3,124 በየዓመቱ ይሰጣቸዋል። ሁሉም የሕዝብ ቻርተር ት/ቤቶች እንደ ተማሪው የትምህርት ውጤት፣ ወይም እንደ ልዩ ትኩረት አስፈላጊነቱና ሁኔታ፣ አልያም በሌላ ምክንያት ላይ የተመረኮዘ አበል በእያንዳንዱ ተማሪ ልክ ይቀበላሉ። የJuly 1–June 30 የበጀት ዓመትን ተከትሎ ት/ቤቶች በሩብ ዓመት መደብ ከDC አስተዳደራዊ መንግስት ድጎማ ይቀበላሉ፤ የመጀመሪያው ክፍያ የሚሰጠውም July 15 ላይ ነው።