ከቻርተር ግምገማ ሊገኙ የሚችሉ ውጤቶች ምንድን ናቸው?

የት/ቤቱን የቻርተር ግምገማ ሪፖርት ከተመለከተ በሗላ የDC PCSB ቦርድ የት/ቤቱ ቻርተር እንዲቀጥል ወይም እንዲቋረጥ በድምጽ ምርጫ ይወስናል። በSchool Reform Act ወይም SRA መሰረት የPCSB ቦርድ በዚህ ውሳኔ ላይ በራስ የመወሰን ፍቃድ ተሰጥቶታል: ቦርዱ ት/ቤቱ ግቦቹን ሙሉ በሙሉ እንዳልተወጣ አልያም የንብረት ህግ መተላለፍን እንደፈጸመ ከተረዳ የት/ቤቱን ቻርተር ለመሻር ወይ ደግሞ እንዲቀጥል ለመፍቀድ መምረጥ ይችላል፤ ይህ ውሳኔ ቅደም ሁኔታ ሊኖረውም ላይኖረውም ይችላል።