አንድ አመልካች የትርፍ አልባ መደብ እንዲሰጠው ማሟላት ያለበት መስፈርቶች ምንድን ናቸው?

በDistrict of Columbia Nonprofit Corporation Act, Title 29, የD.C Code Chapter 4 መሰረት ሙሉ ተቀባይነትን ለማግኘት የሚሻ ማንኛውም የሕዝብ ቻርተር ት/ቤት አንደ ትርፍ አልባ ድርጅት መዋቀር አለበት፤ ይህ እንዳለ ሆኖ ሂደታቸውን ጀምረው በግዜው መደብ አፕሊኬሽን ማስገባት ላልቻሉ አንዳንድ አመልካቾች ቅደመ ሁኔታ ተሰጥቷቸው ቻርተራቸው ሊጸድቅ ይችላል። እንዲህ አይነት ሁኔታ ሲያጋጥም አፕሊኬሽኑ ተቀባይነት እንዲያገኝ የአመልካቹ መካተታቸውን ማጠናቀቅ መሟላት ያለበት ቅደመ ሁኔታ ነው።