አንድ ት/ቤት ከቻርተር ግምገማ በፊት የቻርተሩን ዓላማና ውጥን መለወጥ ይችላል?

አንድ ት/ቤት ቻርተሩን ለማሻሻል በተፈለገው ግዜ ማመልከቻ ማስገባት የሚችል ቢሆንም፤ ጥያቄው የቀረበበት ግዜ ት/ቤቱ ስራውን የጀመረበት 15ኛው ወይም 30ኛው ዓመት ከመሙላቱ ሁለት ዓመት አስቀድሞ፣ ወይም የት/ቤቱ 5ኛ፣ 10ኛ፣ 20ኛ ወይም 25ኛ ግምገማ ዓመት ከመድረሱ አንድ ዓመት አስቀድሞ ካልሆነ በቀር አብዛኛውን ጊዜ DC PCSB የት/ቤቱ ዓላማና ውጥን እንዲቀየሩ ፍቃድ አይሰጥም። የPerformance Management Framework ወይምPMFን እንደ ራሱ ቻርተር ዓላማና ውጥን ወስዶ ለማጽደቅ የወሰነ ት/ቤት ግን የላይኛው መስፈርት አይመለከተውም። PMFን እንደ ዓላማ መርሕ የማጽደቅን ውሳኔ ተከትሎ (መርሑን እዚህይመልከቱ)፣ የቻርተር ት/ቤቱ አገልግሎት ከጀመረበት ከ15ኛውወይም ከ30ኛው ዓመት በኋላ ባሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ወይም ከት/ቤቱ ግምገማ በኋላ ባለው አንድ ዓመት ውስጥ ማሻሻያው እንዲካሄድ DC PCSB ፍቃድ መስጠት ይችላል።
መርሑን እዚህ ተመልከቱ። የቻርተር ማሻሻያ አዘገጃጀት መመሪያ ከፈለጉ እዚህ ይመልከቱ።