አንዳንድ የሕዝብ ቻርተር ት ቤቶች ለምን ይዘጋሉ?

ት/ቤቶች ቻርተራቸው የሚሻርበት 3 አበይት ምክንያቶች አሉ። የመጀመሪያውም ት/ቤቱ የቻርተር ዓላማውን ሊያሳካ አለመቻሉ ነው። ለምሳሌ፥ ት/ቤቱ የትምህርታዊ ስኬት ዓላማውን ከግብ ካላደረሰ፣ በDC School Reform Act of 1995 (SRA) መሰረት ለቻርተር እደሳ የሚያበቃውን መስፈርት አያሟላም። ሁለተኛው ምክንያት ት/ቤቱ ለህግ የማይታዘዝ ሆኖ ከተገኘ ነው። ሶስተኛው ምክንያት አሉባልታዊ የበጀት አጠቃቀምን ይመለከታል። የSchool Reform Actን መሰረት አድርጎ አንድ ት/ቤት ተከታታይ አሉባልታዊ የበጀት አጠቃቀም ከታየበት PCSB Board የት/ቤቱን ቻርተር መሻር አለበት፤ እንዲሁም ት/ቤቱ የተግባራዊ ህግ መጣስ ከተገኘበት ቻርተሩ ሊሻር ይችላል።