ነባር ት/ቤቶች የቻርተር ት/ቤት ለመሆን መጠየቅ ይችላሉ?

አዎ። መስፈርቱን ያሟላ አመልካች አፕሊኬሽን በማስገባት፥ 1) በDistrict of Columbia የሚገኝን የሕዝብ ት/ቤት ወደ ሕዝብ ቻርተር ት/ቤት መቀየር 2) የግል ወይም ገለልተኛ የሆነን ት/ቤት ውደ ሕዝብ ቻርተር ት/ቤት መቀየር ወይም 3) አዲስ የሕዝብ ቻርተር ት/ቤት ማቋቋም ይችላል። ከነበሩበት የሚለወጡ ት/ቤቶች በD.C. ኮድ § 38-1802.01 ስር የሚገኙትን ተጨማሪ መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።